አለም አቀፍ የኤድስ ቀንን ምክንያት በማድረግ ህዳር 22 ቀን 2003 ዓ.ም የሲቪል ሰርቪስ እና የሥራ አመራር ተቋም ሠራተኞች በጋራ በዓሉን በደመቀ ሁኔታ አክብረዋል፡፡ አቶ ዳንኤል ባልቻ የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የዘርፈ ብዙ ኤች.አይ.ቪ.ኤድስ ምላሽ ማስተባበርና መምራት ደጋፊ የሥራ ሂደት ኦፊሰር እንኳን ለ22ኛ ጊዜ የሚከበረው የዓለም ኤድስ ቀን አደረሳችሁ ካሉ በኋላ ይህ በሽታ ባለፈው ዘመናት በርካታ ዜጐችን ያሳጣን ከመሆኑም በላይ
ለውስብስብ አስከፊ ችግሮች የዳረገን በመሆኑ ይህንን አስከፊ በሽታ ለመከላከል እንዲሁም ስርጭቱ እንዲቀንስ የመሪነት ደረጃን በሁሉም በኩል በማካሄድ ዜጐች በኤች.አይ.ቪ እንዳይያዙ የበኩላችንን አስተዋፅዖ ማድረግ አለብን ብለው የዕለቱን ኘሮግራም በማስተዋወቅ የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ተፈራ መስቀሌ በዓሉን በንግግር እንዲከፍቱ ጋብዘዋል፡፡...... ተጨማሪ>>
ጥር 9 / 2002ዓም>>
ከዞን ወረዳና ልዩ ወረዳ ለተውጣጡ አመራሮች ስልጠና ተሰጠ
በክልል ውስጥ ካሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ለተውጣጡ በየደረጃው ያሉ የአስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ጸሀፊዎች ከ19-28/04/02 ለአስር ተከታታይ ቀናት በስራ አመራር አዳራሽ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ ፡፡ ስልጠናው በዋናነት ያተኮረው በኋላ ቀር አሰራር ሲሰጥ የቆየውን አገልግሎት አሰጣጥ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመተካት መረጃዎችን በአግባቡ ለመያዝና በወቅቱ ለማስተላለፍ የሚያስችል እውቀት ለመጨበጥ እንዲያስችል መሆኑ ታውቋል ፡፡ ... ተጨማሪ>>