f  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

 
 
Last Updated Wednesday, June 8, 2011 5:26 PM
note

ጥር 9 / 2002ዓም>>>

 newከዞን ወረዳና ልዩ ወረዳ ለተውጣጡ አመራሮች ስልጠና ተሰጠ

 

headlineየሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የለውጥ ፕሮግራሞችና ፓከጆች ጥናትና ትግበራ ዋና የስራ ሂደት አስተባሪነት በደቡብ ክልል ከሚገኙ ዞኖች ወረዳዎችና ልዩ ወረዳዎች ለተውጣጡ ቁጥራቸው ከአምስት ሺህ በላይ ለሆኑ አመራሮች በሚዛናዊ ውጤት ተኮር ስርዓት/BSC/ ዙሪያ በ04/04/03 የአንድ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በየዞን ማዕከላት ተሰጥቷል ፡በሲዳማ ዞን ከሚገኙ ዞኖችና ወረዳዎች ለተውጣጡ አመራሮች በሀዋሳ ሲዳማ ባህል አዳራሽ   የክልሉ ቴክኒካል አማካሪ ቲም አባል የሆኑት አቶ አማረ ሺፈራው ተሰጥቷል ፡፤

በውይይቱም ላይ  የተሳተፉት  በሀገሪቱ ውስጥ ካሉ የከፍተኛ ት/ት ዘርፍ /በምህንድስናው በኢንጂነሪንጉ/ ዘርፍ የሚወክሉ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ያሉት ፋካሊቲ ኢንስትቲዩት እና ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት (institute of technology) የሚባለውን የሚወክሉና  እነርሡም አዳማ ፣ መቀሌ፣ ባህር ዳር፣ አዋሣ፣ አዲስ አበባ፣ ሆሮማያ እና ጅማ ዩኒቨርሲቲዎች ሲሆኑ እንዲሁም ከፌዴራል ተቋማት የተለያዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች፣ ከሀገር ውስጥና ስራውን አብረው የሚሰሩ ከውጪ የመጡ ጀርመናውያን ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡ በፌደራል የፕሮግራሙ አስተባባሪ የሆኑት ዶክተር መብራቱ መለስ እንደገለጹት ይህ ሀገራዊ የምክክር መድረክ የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ለመገምገም የተካሄደ ሲሆን አላማውም፡- በመጀመሪያው ዙር የጋራ መድረክ ላይ በጋራ የፀደቁ እቅዶችን አፈፃፀምና የአካሄድ ልምዶች ያሏቸውን ተሞክሮዎች እንዴት ወደ ሌላው ማስፋት እንደሚቻልና እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችን ከፍተኛ ትኩረት አካሂዶ በመወያየት ለቀጣይ አፈፃፀም እንዴት ለመፍታት እንደሚያስችል ፡ ያላቸውን ተሞክሮዎች የልምድ ልውውጥ ተደርጓል፡፡ በመጀመሪያውም የአፈፃፀም ሪፖርቶች በፌደራል ተቋሙ በኢንጂነሪንግ ካፖሲቲ ፕሮግራም በሚባለው የቀረበ ሲሆን በመቀጠልም ዩኒቨርሲቲዎች አፈፃፀማቸውን ካቀረቡ በኋላ የstudy program reform በመማር ማስተማር ካሪከረለም (teaching learning, curriculum) ያለው አፈፃፀም ምን እንደሚመስል፣ የመልካም አስተዳደር እጦት በዩኒቨርሲቲዎች የሚንፀባረቅ በመሆኑ ይህንን ለመፍታትና የቴክኖሎጂ ሽግግር በሚሉትን ርእሶች የለውጥ ፕሮግራም ለመስራት መሪዎች በመከፋፈል በእነዚህ በ3 በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የቡድን ውይይት ተካሂዷል፡፡ በሪፖርቱ ከቀረቡት ዋና ዋና ችግሮች ይህን የለውጥ ፕሮግራም ለመተግበር መሪዎች የማምጣት ትልቁ ሥራ ቢሆንም በለውጡ ፕሮግራም ከሚሣተፉ 8 ኢንስትቲዩት ውስጥ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኢንስትቲዩት እና ቴክስታይል ጋርመንገድ እና ፋሽን ዲዛይን አንድ ፕሮፌሰር እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሠር መጥተው ስራቸውን የጀመሩ እንደሆነ እና ይህም የመልካም አስተዳደር እጦት የሚፈታበት አንዱ መንገድ መሆኑንም ጭምር ተገልጿል፡፡ በአጠቃላይ በዩኒቨርሲቱዎች ብዙ ፋካሊቲዎች ዲፖርትመንቶች እንዳሉ ሁሉ ብዙ ችግሮች መኖራቸው ቢታወቅም እነዚህን ሙሉ በሙሉ ነፃነት እንዲያገኙ የሚደግ ስራ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም ይላሉ እንደዶክተሩ ገለጻ ሌላው የሚታወቀው ቁልፍ ችግራችን የመፈፀም አቅም ሪሶርስ እያለን ስራ ላይ ለማዋል ችግሮች ሲሆን መንግስት ከፍተኛ ሀብት መድቦ የገዛቸው የላብራቶሪ ኢኩፕመንቶች፣ ማሽኖች የመሣሰሉትን ጠግኖ ስራ ላይ የማዋል ችግሮች ቢታይም ዩኒቨርስቲ እነዚህን ወደ ስራ በአግባቡ በመጠቀም ስራ ላይ በማዋል ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልጸዋል፡: በመጨረሻው በሚቀጥለው በ3ኛ ሩብ አመት እንዴት መሄድ እንደለባቸው በወመያየት አነዚህ አራት ዘርፎች ተመጋግበው የሚተገበሩ መሆናቸውና የመጨረሻ ግባቸው የሀገራችንን ኢንዱስትሪዎች በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 
News....Start from the Latest <<Prev 1 2 3 4 5 6 . . Next>>
Copyright © SNNPR CBB 20010 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official SNNPR Capacity Building Website