f  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

 
 
Last Updated Friday, December 24, 2010 3:58 PM
note

ጥር 6 / 2002ዓም>>>

 new በኢንተርፕሪነርሺፕ ዙሪያ ወርክሾፕ ተካሄደ ::

headlineበክልሉ ኢኮቴ ቢዝነስ ኢንኩቤሽን ሴንተር (የግል ሥራ ፈጠራ ማዕከል) አስተባባሪነት ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኢንኩቤሽን ሴንተር እና ደቡብ ብሔር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግሥት ኢንኩቤሽን ሴንተር ለተውጣጡ ሰልጣኞች በሥራ ፈጣሪነት /ENTERPRENAIRSHIP// ዙሪያ ከ03/05/02-06/05/02 ለአራት ተከታታይ ቀናት የቆየ ወርክሾፕ በሥራ አመራር ተቋም ተከሂዷል፡፡

ስልጠናው ዓላማ ያደረገው በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ እውቀት ያላቸው ባለሙያዎች ትምህርታቸውን ከከፍተኛ ተቋም አጠናቀው የመንግስት ተቋማትን ብቻ ጠብቀው የሚቀጠሩበትን ሁኔታ በመቀነስ ባለሙያዎች ተደራጅተው ሥራ ፈጣሪ በመሆን ተገቢውን ሃገራዊ የዜግነት ድርሻ እንዲወጡ ለማድረግ የሚደግፍ ማዕከል ተቋቁሞ ተቋማዊ መሰረቱ ተደራጅቶ ወደ ትግበራ ለማስገባት መደበኛ ስራውን በማከናወን ላይ በመሆኑ ስራ ፈጣሪ መሆን የሚያስችላቸውን አቅም ለመፍጠር እንደሆነ ተገልጻል ፡፡ ለ45 ሰልጣኞች የተሰጠው ወርክሾፕ በ software development, maintenance, Computer training ዙሪያ መሆኑም ታውቋል ፡፡ አቶ ታገሰ ታገለ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ እንደገለጹት ከደቡብ ኢኮቴ ኢንኩቤሽን ሴንተር 12 ካምፓኒ እንዲሁም ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቴ ኢኮቴ ኢንኩቤሽን ሴንተር 5 ካምፓኒ በድምሩ 17 ካምፓኒዎችን ተቀብለን በማህበር ለተደራጁ አባላት ባዘጋጀነው ቢሮና ቁሳቁስ የራሳቸውን ሥራ በመስራት ገቢ እንዲያገኙ የማድረግ ተግባር እያከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡ ስልጠናውን የሰጡት ዶ/ር/ ወሮታው በዛብህ እና ሚ/ር ¼ንዝ አር ሬድ ላየን ናቸው ፡፡
አቶ አይናለም ፀጋዬ የኢኮቴ ኤጀንሲ ሥራ አስኪያጅ በስልጠናው ማብቂያ ለተሳታፊዎች የተዘጋጀውን የምስክር ወረቀት ከሰጡ በኋላ ባሰሙት ንግግር ነገ ተስፋ ጥለን የምንጠብቃችሁ የነገ ባለሃብት ወጣቶች በቅድሚያ እንኳን ለዚህ ቀን አበቃችሁ ካሉ በኋላ ሃገራችን ከድህነት አዘቅት የምትወጣው በመንግስት ላይ ብቻ ተስፋ በመጣል የጠባቂነት መንፈስ በማዳበር ሳይሆን በራሳችን በመተማመንና ቆራጥና ራዕይ ያለው በመሆን ሃገራችን የምትመካብን ዜጋ ልንሆን ይገባል ብለዋል ፡፡ አያዘውም በፈጣን ለውጥ ላይ ባለች ዓለም ውስጥ ተወዳዳሪ ለመሆን በክልላችን ውስጥ ባሉ በርካታ ዞኖችና ወረዳዎች ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ለማሳፋፋት የሜይንቴናንስ ' ኔትወርኪንግ'ሶፍትዌር ስራዎች በብዛት የሚፈለጉ በመሆኑ ይህንን ቴክኖሎጂ ህብረተሰቡ ዘንድ ለማድረስ የግል ተቋማት ወሳኝ በመሆናቸው ለዚሁ ተግባር ዩኒቨርሲቲዎችና የግል ተቋማት በርካታ የኢኮቴ ባለሙያዎችን እያፈሩ በመሆኑ በርካተተመራቂዎች ትምህርታቸውን ጨርሰው ሲወጡ ስራ አጥ እንዳይሆኑ የግል ተቋማት መፈጠር ወሳኝ ሚና የሚጫወት በመሆኑ ፈቃድ፤ አማካሪና የምትሰሩበት ቦታ የተዘጋጀላችሁ በመሆኑ ጠንክራችሁ መስራት ይገባችኋል ሲሉ መልካም የስራ ዘመን በመመኘት ስልጠናው ተጠናቋል፡፡

 
News....Start from the Latest <<Prev 1 2 3 4 5 6 . . Next>>
Copyright © SNNPR CBB 20010 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official SNNPR Capacity Building Website