f  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

 
 
Last Updated Friday, December 24, 2010 3:58 PM
note

ጥር 2002ዓም>>>

 new በአቅም ግንባታ ሴክተር ሰራተኞች ለአረጋውያን ድጋፍ አደረጉ::

headline በአቅም ግንባታ ሴክተር የዘርፈ ብዙ የኤች አይ ቪ ኤድስ ምላሽ ማስተባበርና መምራት ደጋፊ የስራ ሂደት አስተባባሪነት በደቡብ ክልል ውስጥ /መድን ኢትዮጵያ ፖዘቲቭ አረጋዊያን ማህበር/ በሚል ስያሜ በማህበር ተደራጅተው በመንቀሳቀስ ላይ ላሉ 81 አረጋውያን የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ በዋርካ ሆቴል የምሳ ግብዣ የተደረገላቸው ሲሆን ከአቅም ግንባታ ሴክተር (አቅም ግንባታ ቢሮ' ሥራ አመራር ተቋም' ሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ እና ኢኮቴ ኤጀንሲ) ሰራተኞች የተሰበሰበ አልባሳት ስጦታ ተበርክቷል ፡፡

አቶ ሚልኪያስ እስራኤል የአቅም ግንባታ ሴክተር የመንግስት ኮሚኒኬሽን የስራ ሂደት ባለቤት በፕሮግራሙ መክፈቻ ባሰሙት ንግግር ጥሪያችንን አክብራችሁ እዚህ በመገኘታችሁ በሴክተሩ ስም ምስጋናዩን አቀርባለሁ ካሉ በኋላ ይህ ዛሬ የተደረገው ድጋፍ መጠነኛ ቢሆንም በቀጣይ አቅም በፈቀደ መጠን ከጎናችሁ እንሰለፋለን ሆኖም የማህበሩ አባላት ሥራ ፈጣሪ በመሆን በተቻለ መጠን ራሳችሁን የመቻል ተግባር ማከናወን ይጠበቅባችኋል ብለዋል ፡፡ ወ/ሮ ሙሉ ጥሩነህ የጸረ ኤች አይ ቪ ሜይንስትሪሚንግ ኦፊሰር የእለቱን የድርጊት መርሃ ግብር እና ዓላማ አስመልክተው ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች ገለጻ ያደረጉ ሲሆን የተሰበሰበውንም አልባሳት ለተወካዩ አስረክበዋል ፡፡ አቶ አብረሃም ነጋ / መድን ኢትዮጵያ/ ፖዘቲቭ አረጋውያን ማህበር ሊቀመንበር ስለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው በቀጣይም ቢሮው ከጎናቸው በመሰለፍ አቅማቸውን የመገንባት ተግባር እንዲያከናውን ጥሪ አቅርበው ከሰራተኞች የተሰበሰበውን አልባሳትና መጠነኛ ገንዘብ ድጋፍ ተረክበው ፕሮግራሙ ተጠናቋል ፡፡

 
News....Start from the Latest <<Prev 1 2 3 4 5 6 . . Next>>
Copyright © SNNPR CBB 20010 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official SNNPR Capacity Building Website