ታህሳስ 28 / 2002ዓም>>>
በክልል ውስጥ ካሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ለተውጣጡ በየደረጃው ያሉ የአስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ጸሀፊዎች ከ19-28/04/02 ለአስር ተከታታይ ቀናት በስራ አመራር አዳራሽ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ ፡፡ ስልጠናው በዋናነት ያተኮረው በኋላ ቀር አሰራር ሲሰጥ የቆየውን አገልግሎት አሰጣጥ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመተካት መረጃዎችን በአግባቡ ለመያዝና በወቅቱ ለማስተላለፍ የሚያስችል እውቀት ለመጨበጥ እንዲያስችል መሆኑ ታውቋል ፡፡
ይ¤ው በኢኮቴ የሥራ ሂደት ፈጻሚዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በተግባር የታገዘ በመሆኑና መሰረታዊ የኮምፒዩዊተር እና የኢንተርኔት አጠቃቀም እውቀት ያስጨበጠ ስልጠና በመሆኑ እንዲሁም በብቁ አሰልጣኞች የተሰጠ በመሆኑ ወደ ተግባር ስንገባ ለስራችን አጋዥ ሃይል አግኝተናል ሲሉ ሰልጣኞቹ የገለጹ ሲሆን ይ¤ው ተግባር አገልግሎቱን ላላገኙ ወረዳዎች ቢሰጥና ስልጠናው ተከታታይነት ያለው ቢሆን የሚፈለገው ውጠት ላይ መድረስ ይቻላል የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡በስልጠናው ከክልል ከዞን ከወረዳና ልዩ ወረዳ የተውጣጡ 169 ሴቶች ተሳትፈዋል፡፡ አቶ ዓይናለም ጸጋዬ የኢኮቴ ኤጀንሲ ሥራ አስኪያጅ በስልጠናው ማብቂያ ለሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ከሰጡ በኋላ ባሰሙት ንግግር በክልላችን በጣም ሩቅ የሚባሉት እንደ ሱርማ እና ዳሰነች የመሳሰሉ አካባቢዎች የቪዲዮ ኮንፍረንስና መሰል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎች ሲሆኑ በክልላችን ባሉ 30 አዲስ ወረዳዎችም ቴክኖሎጂ ለማስፋፋት አዳዲስ መሳሪያዎች በመግባታቸው በቅርቡ እነሱም ተጠቃሚዎች የሚሆኑበት ሁኔታ ተመቻችቷል ብለዋል፡፡ አያይዘውም አብዛኛው ሰልጣኝ ኮምፒዩተርን ከጽሁፍ ባለፈ ሁኔታ የመጠቀም እውቀት ያላገኘ በመሆኑ መረጃዎችን የማደራጀት መሰረታዊ አቶ ሙደር ሰማን የደኢህዴን ጽ/ቤት የሰው ኃይል አስተዳደር ሃላፊ በስልጠናው ማብቂያ በሰጡት አስተያየት የዚህ ስልጠና ዋንኛው ዓላማ ኋላ ቀር በሆነው የመረጃ አያያዝ የነበረውን ችግር ለመቅረፍ ታስቦ ነው ካሉ በኋላ ይህንን ችግር ለመቅረፍ የክልሉን ኢኮቴ ኤጀንሲ እገዛ ጠይቀን የሰው ሃይል ማብቃትና የመሳሪያ ድጋፍ እውቀት እንድታገኙ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና በመሆኑ ለተግባራዊነቱ የእናንተን ጥረት ይጠይቃል ካሉ በኋላ በብዙ ወጪ ተገዝቶ የመጣው የቴክኖሎጂ መሳሪያ በአግባቡ በጥቅም ላይ እንዲውሉ አገልግሎት ላይ መዋል እንዳለባቸው ገልጸው እንኳን ደስ ያላችሁ መልካም የስራ ዘመን ይሁንላችሁ ብለዋል፡፡ የተደረገልን ሲሆን ይህው ተግባር ጅምር ቢሆንም በቀጣይ ተመሳሳይ ድጋፍ ከኤጀንሲው እንጠብቃለን ካሉ በኋላ የክልሉ ኢኮቴ ኤጀንሲን እንዲሁም የኤጀንሲውን ስራ አስኪያጅ አቶ አይናለም ጸጋዬ ላደረጉት ድጋፍ በድርጅቱ ስም አመስግነው ስልጠናው ተጠናቋል ፡፡