f  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

 
 
Last Updated Friday, December 24, 2010 3:58 PM
note

ታህሳስ 17 / 2002ዓም>>>

 new በክልሉ ለሚገኙ ሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ ባለሙያዎቸ የአሰልጣኖች ስልጠና ተሰጠ::

headlineየክልሉ አቅም ግንባታ ቢሮ ሐምሌ 29/2001 ዓ.ም በሥራ አመራር የስልጠና አዳራሽ አመታዊ ጉባዔውን አካሄደ፡፡ ጉባኤው ለሁለት ተከታታይ ቀናት የቆየ ሲሆን በአቅም ግንባታ ቢሮ ያሉ የስራ ሂደት ባለቤቶች፣ የ13 ዞኖችና የ8 ልዩ ወረዳዎች አቅም ግንባታ ሀላፊዎች የጉባዔው ተሳታፊ ሆነዋል፡፡...

አቶ ተስፋዬ ኪዳነ ማርያም የሲቪል ሰርቪስ ኤጄንሲ ሥራ አስኪያጅ ስልጠናውን ሲከፍቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ካደረጉ በኋላ ሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ በሶስት ዋና የስራ ሂደት ራሱን ችሎ ከተደራጀ በኋላ ተጠሪነቱ ለአቅም ግንባታ ቢሮ ሆኖ በአዲስ መልክ በአዋጅ ተቋቁሞ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከነዚህም አንዱና ወሳኝ የስራ ሂደት የሆነው የሰው ሃብት መረጃና ስታትስቲክስ አቅርቦት ዋና የስራ ሂደት የሙከራ ትግበራ ሲካሄድ ቆይቶ ወደ ሙሉ ትግበራ የተገባ በመሆኑ ለዚሁ ስራ አጋዥ ይሆን ዘንድ የአሰልጣኞች ስልጠና መሰጠት አስፈላጊ በመሆኑ ይህ የአሰልጣኞች ስልጠና ተዘጋጅቷል ሲሉ ገልጸዋል ፡፡ አያይዘውም በዚህ ስልጠና ቁጥራቸው እስከ 300 የሚደርስ ሰልጣኞች እንደሚሳተፉ የታወቀ ሲሆን ከዚህ ስልጠና በኋላ በ13 ዞኖች' በ134 ወረዳዎችና ልዩ ወረዳዎች ለፈጻሚዎች የ6 ቀናት ስልጠና ይሰጣል ብለዋል:: እንደ ሃላፊው አገላለጽ በክልላችን 130.000 የሚደርሱ የመንግስት ሰራተኞች የሚገኙ ሲሆን የነዚህ ሰራተኞች መረጃ ትክክለኛና ተዓማኒ በሆነ መልኩ ዳታ ቤዝ ፈጥሮ መስራት አስፈላጊ በመሆኑ ይ¤ው ዘመናዊ የሆነው የመረጃ አያያዝ /ዳታ ቤዝ / ስራ ተጀምሮ በዚህ አመት እንደሚጠናቀቅ ይገመታል ካሉ በኋላ ኤጀንሲው ከዚህ በኋላ እስከ ታች ድረስ ወርዶ የመደገፍና ክትትል የማድረግ ግዴታ ስላለበት በርካታ ስራዎችን በጋራ የመስራት ሁኔታ ተመቻችቷል ብለዋል ፡፡ በመጨረሻም በዚህ የስድስት ቀን ስልጠና የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ግንዛቤ ጨብጣችሁ ውጤታማ ስራ እንድትሰሩ ሲሉ አሳስበው ስልጠናው በይፋ መከፈቱን አብስረዋል ፡፡ በዕለቱ ስልጠናውን የሰጡት አቶ ዳዊት ፍቅሬ የሰው ሀብት መረጃና ስተታስቲክስ አቅርቦት ዋና የስራ ሂደት ባለቤት ሲሆኑ የስልጠናውን ይዘት' የስራ አደረጃጀት አመጣጥና ዕድገት ገለጻ አድርገው ወደ ሰልጠናው ገብተዋል፡፡

 
News....Start from the Latest <<Prev 1 2 3 4 5 6 . . Next>>
Copyright © SNNPR CBB 20010 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official SNNPR Capacity Building Website