የካቲት 25 / 2002ዓም>>
በኘሮግራሙ መሠረት አቶ ዘላለም አሸናፊ የደቡብ ኢትዮጵያ ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው ማህበር አባል የሆኑት የህይወት ተሞክሮዋቸውን “በማቅረብ በመመርመር ራሳችንን እንወቅ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ደቡብ ኢትዮጵያ ኤች.አይ.ቪ ፖዘቲቭ ወጣቶች ማህበርም የተለያዩ አዝናኝና ቀስቃሽ የሆኑ ዜማዎችንና ድራማዎችን አስተላልፈዋል፡፡