መስከረም 10 / 2003ዓም>>
በውጤት ተኮር ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናውን የሠጡት የክልሉ አማካሪ ቲም አባል የሆኑት አቶ በላይ አበበና አቶ ፍቃዱ ተክለ ማርያም ናቸው፡፡ የስልጠናውን ይዘት በተመለከተ ከደረጃ አንድ ስድስት የውጤት ተኮር ዕቅድ ግንባታ፣ ከደረጃ ሰባት እስከ ዘጠኝ የውጤት ተኮር ትግበራ እንዲሁም ስለ መሠረታዊ የአሰራር ለውጥ ማብራሪያን ያካተተ እንደሚሆን በስልጠናው ሂደት ተገልጿል፡፡
በመጨረሻም የአፈፃፀም አመራርን የተገነዘበ፣ የሚዛናዊ የውጤት ተኮር ምንነትና አፈፃፀምን የተረዳ አመራር መፍጠር መቻል ከስልጠናው የሚጠበቁ ውጤቶች እንደሆኑ ከአሠልጣኞች ከተሠጠው ማብራሪያ መረዳት ተችሏል፡፡ በስልጠናው ከ15ዐ በላይ ኃላፊዎች መሳተፋቸው ታውቋል፡፡