f  
ethiopiaflag snnprslag
   

 

 
Last Updated Friday, December 24, 2010 9:18 PM
note
 

የመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የወጪ መጋራትን በተመለከተ የቀረበ ትምህርታዊ ፅሁፍ


በሀገራችን የከፍተኛ ትምህርት ፍላጎት በጣም እያደገ በመምጣቱና የተማሪዎችም ቁጥር መጨመሩ የኑሮ ውድነትና የተፈላጊ ቁሳቁሶችም ዋጋ እየናረ በመሄዱ መንግስት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚመድበው በጀት ከመጠን በላይ ከመሄዱም በላይ ተጨማሪ ዜጎችን በብዛትና በጥራት በተለያዩ የትምህርትና የሙያ መስኮች በመንግስት አቅም ብቻ ማሰልጠን /ማስተማር/ የማይቻልበት ደረጃ ላይ መድረሱን በዚህ መስክ የተደረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

የሚኒስተሮች ም/ቤት ባወጣው ደንብ ቁጥር አንቀጽ 154/2000 እና አንቀጽ 4/5 መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጪ መጋራት ማለት በፌደራል መንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው የሚማሩ በዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆኑ ተጠቃሚዎችን መንግስት ለትምህርትና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚያወጣውን ወጪ የሚጋሩበት ስርዓት ነው፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ሚዛናዊ በሆነ መልክ የከፍተኛ ትምህርትን በጥራት ለማዳረስ እና የመንግስት አቅም ለማጎልበት ለከፍተኛ ትምህርት ተጠቃሚዎች የመንግስትን ወጪ በተወሰነ መጠን እንዲጋሩ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት ለተግባራዊነቱ የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 3/251/1995 እና ደንብ ቁጥር 325/1995 እንዲሁም የአፈፃፀም መመሪያ እንዲወጣለት ተደርጓል፡፡ Read More>>

 

የተጨማሪ እሴት ታክስ ሕግና የአፈፃፀም አቅጣጫ ማብራሪያ

የተጨማሪ እሴት ታክስ ቀደም ሲል ሥራ ላይ የነበረውን በሀገር ውስጥ በሚመረቱና ከውጭ ወደ አገር በሚገቡ ዕቃዎችና በሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ይሰበሰብ የነበረውን የሽያጭ ታክስ በመተካት ከታህሣሥ 23 ቀን 1995 ዓ/ም ጀምሮ ሥራ ላይ የዋለ ቀጥታ ያልሆነ የታክስ ዓይነት ነው፡፡ ታክሱ አዲስ ሳይሆን ቀደም ሲል በነበረው የሽያጭ ታክስ ተተክቶ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን አዲስነቱ በኮምፒዩተር የታገዘ፣ በምርትና በስርጭት ሂደት ውስጥ በተጨማሪ እሴት ላይ ብቻ የሚታሰብ፣ ዘመናዊና በደረሰኝ አጠቃቀም ላይ በተመሠረተ የታክስ አሰባሰብ ዘዴ የሚመራ በመሆኑ ብቻ ነው፡፡

የተጨማሪ እሴት ታክስ (Value Added Tax - VAT) መሠረቱ ሰፊ የሆነ በፍጆታ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ላይ የሚጣል የታክስ ዓይነት ነው፡፡ ታክሱ ከአስመጪዎችና ጥሬ ዕቃ አምራቾች አንስቶ እስከ ችርቻሮዎች ድረስ በሚደረጉ የማምረትና የማከፋፈል /የማሠራጨት/ ሂደቶች በሁሉም ደረጃዎች በሚፈጠረው ተጨማሪ እሴት ላይ ብቻ ተመስርቶ በማስላት ይሰበሰባል፡፡ በዚህም ምክንያት፣

        • ምርት ከአንድ ደረጃ ወደ ሌላው በሚተላለፍበት ወቅት የሚፈጠርን የታክስ ተንከባላይነት ባህሪይ ቀደም ብሎ የተከፈለውን ታክስ የማቀናነስ ስልት በመከተል በታክስ ላይ ታክስ የማሰብ ሁኔታ እንዳይፈጠር ያደርጋል፣
        • የነበረው የሽያጭ ታክስ በጥሬ ዕቃ ላይ የተከፈለን ታክስ ብቻ ተመላሽ የሚያደርግ ሲሆን፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ ግን ለማምረቻ መሣሪያዎች፣ ለማከፋፈልና ለአስተዳደራዊ ተግባራት የተከፈለ ታክስን ጭምር ተመላሽ ያደርጋል፣
        • ወደ ውጭ በሚላኩ ምርቶች ላይ ተፈጻሚ የሚሆነው ምጣኔ (Rate) ዜሮ በመቶ(ዐ%) ስለሆነና ለግብዓቶች የተከፈለው ታክስም ተመላሽ የሚደረግ በመሆኑ የወጪ ንግድ እንዲበረታታ ያደርጋል፡፡

የተጨማሪ እሴት ታክስ አፈጻጸም በደረሰኝ ላይ ተመስርቶ የሚከናወን በመሆኑ በቀላሉ ሳይከፈል ሊታለፍ ወይም ሊጭበረበር የሚችል ታክስ ባለመሆኑ የታክስ ሥወራንና ማጭበርበርን በመቀነስ በታክስ ሕግ አፈጻጸም ሊኖር የሚገባውን ውጤታማነትና ፍትሐዊነት በአግባቡ ያስጠብቃል፡፡

በተጨማሪ እሴት ታክስ ትግበራ አነስተኛ ገቢ ባላቸው የሕብረተሰቡ ክፍሎች ላይ ሚዛናዊ ያልሆነ ጫና እንዳይፈጥር ታስቦ ለኑሮ መሠረታዊ የሆኑ የፍጆታ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ከታክሱ ነጻ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡
ከዚሁ አስተሳሰብ አኳያ የሚከተሉት አቅርቦቶች ከታክሱ ነጻ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡

        • ቢያንስ ሁለት ዓመት ያገለገለ መኖሪያ ቤት ሽያጭ እና የመኖሪያ ቤት ኪራይ፣
        • የፋይናንስ አገልግሎቶች፣
        • የሕክምና አገልግሎት አቅርቦቶች፣
        • የኤሌክትሪክ፣ የኪሮሲንና የውሃ አገልግሎት¼k¬¹g W¦ bStqR¼
        • የትምህርት አገልግሎት አቅርቦቶች፣
        • የትራንስፖርት አገልግሎቶች፣
        • የፖስታ ቤት ሥራዎችና የሕዝብ ትራንስፖርት፣
        • የጥሬ ወተት፣ የደረቅ ዳቦና የደረቅ የእንጀራ አቅርቦት /ከአዋጁ በኋላ የታከለ/
        • የፈቃድና የምስክር ወረቀት ክፍያዎች ናቸው፡፡

የተጨማሪ እሴት ታክስ በአነስተኛ የንግድ ሥራ የተሠማሩ ነጋዴዎች የማስተዳደር ጫና ሊቀንስ በሚችል መልኩ የተቀየሰ በመሆኑ ታክሱ ያልታከለበት ዓመታዊ የሽያጭ ገቢያቸው ከብር 5ዐዐ.ዐዐዐ. በታች የሆኑት ከዚህ የታክስ ማዕቀፍ ውጭ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡ የታክስን ፍትሐዊነት ለመጠበቅ በተመሣሣይ ወቅት ተግባራዊ የሆነው የማስተካከያ ታክስ (የተርን ኦቨር ታክስ) ከብር 5ዐዐ,ዐዐዐ. በታች አመታዊ የሽያጭ ገቢ ባላቸው ግብር ከፋዮች ላይ ተፈጻሚ ተደርጓል፡፡
 መንግሥት የተጨማሪ እሴት ታክስን በተስተካከለ ሁኔታ ከታህሣሥ 23 ቀን 1995ዓ/ም ጀምሮ ሥራ ላይ ለማዋል የተለያዩ የኀብረተሰብ ክፍሎችን አስተያየት በማሰባሰብ በርካታ ማሻሻያዎች አድርጓል፡፡  ታክሱ ሥራ ላይ ከዋለ ወዲህም በየወቅቱ የአፈጻጸም ሂደቱን እየፈተሸ የማሻሻያ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል፡፡

ተጨማሪ እሴት ታክስ
ይህ ታክስ በፍጆታ ላይ ወይም በተጠቃሚው ወጪ ላይ የተመሠረተ የታክስ ዓይነት ነው፡፡ ታክሱ የሚሰበሰበው ወይም የሚቀረጠው ምርት ከውጭ አገር ወደ አገር ውስጥ ሲገባ /ኢምፖርት ሲደረግ/ ወይም በሀገር ውስጥ ማንኛውም የዕቃና የአገልግሎት ግብይት ሲካሄድ ነው፡፡

ሀ/ የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈልባቸው ግብይቶች የሚባሉት

  • በኢትዮጵያ ውስጥ በከፊል በኢትዮጵያ ውስጥ የተመረቱ አቅርቦቶች፣
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ በሆነ ግብር ከፋይ/ወይም ሌላ ተመዝጋቢ/ በመደበኛም ሆነ መደበኛ ባልሆነ መንገድ የተመረቱ ዕቃዎች ወይም የተሰጡ አገልግሎቶች፣
  • የንግድ ሥራን በማስፋፋት ሂደት የሚሠሩትን፣
  • ከታክሱ ነጻ ወይም በዜሮ ትመና የሚቀረጡ መሆናቸው ተለይተው ያልተገለጹ በመደበኛ 15 በመቶ መጣኔ ታክሱ የሚከፈልባቸው ይሆናል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የተሠሩና ለታክሱ በተመዘገቡ ሰዎች የሚካሄዱ ማናቸውም አቅርቦቶች በታክሱ አዋጅ ነጻ እስካልተደረጉ ድረስ በመደበኛ 15 በመቶ መጣኔ ታክስ የሚከፈልባቸው አቅርቦቶች ናቸው፡፡ የታክሱ ከፋይም ለተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን እስካሟላ ድረስ ግለሰብ፣ ማኀበር፣ ድርጅት ወይም ኩባንያ ሊሆን ይችላል፡፡

ለ/ አቅርቦቶች ከዚህ የታክስ ማዕቀፍ ውጭ ሊሆኑ የሚችሉት

  • የታክሱ ከፋይ ባልሆነ ሰው የተሠሩ ሲሆን፣ ወይም
  • በንግድ ሥራ ወይም የንግድ ሥራን ለማስፋፋት በሚደረግ ሂደት ያልተሠሩ ሆነው ሲገኙ ብቻ  ነው፡፡

ታክስ የሚጣልባቸው አቅርቦቶች /Taxable Supplies/
በንግድ ሥራ ላይ ተሠማርተው ዕቃዎችን የሚሸጡ ከሆነ /የዕቃ አቅርቦት የሚያካሄዱ/ ወይም ለሌላ ሰው አገልግሎት ሰጥተው ክፍያ የሚቀበሉ ከሆነ (የአገልግሎት አቅርቦት ካበረከቱ) እነዚህ አቅርቦቶች ታክስ ሊከፈልባቸው የሚችሉ አቅርቦቶች ይሆናሉ፡፡ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ግብር ከፋዮች ከእነዚህ አቅርቦቶች የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስከፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ለሻጩ የምርት ውጤት ታክስ /Output Tax/ ይሆናል ማለት ነው፡፡

የምርት ውጤት ታክስ (Output Tax)
የምርት ውጤት ታክስ ማለት አንድ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ ሰው ታክሱ የሚከፈልበትን የዕቃ ወይም የአገልግሎት አቅርቦት ለደንበኞቹ ሲሸጥ የሚያስከፍለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ነው፡፡ ታክሱን ማስከፈል የሚችለው ሰው ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ እንደሆነ ብቻ ነው፡፡

የተጨማሪ እሴት ታክስ መጣኔዎች/Rates/:- የተጨማሪ እሴት ታክስ ሁለት የመቅረጫ ምጣኔዎች ይኖሩታል፡፡ እነሱም 15 ከመቶ መደበኛ መጣኔና ዜሮ ከመቶ መጣኔ የሚባሉት ናቸዉ፡፡

ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሆኑ ሌሎች አቅርቦቶች:- በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 8 በዝርዝር ተለይቶ በተደነገገው መሠረት ከታክሱ ነጻ የተደረጉ አቅርቦቶች (ዕቃዎችና አገልግሎቶች) ይኖራሉ፡፡ አንድ ሰው እነዚህን አቅርቦቶች (ዕቃዎችና አገልግሎቶች)  አቅራቢ መሆን አለመሆኑን ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልገዋል፡፡ ምክንያቱም ከታክሱ ነጻ የመሆኑን ያህል በሚገዛቸው ግብዓቶች ላይ የተከፈለ ታክስ ተመላሽ እንዲሆንለት ወይም እንዲታሰብለት መጠየቅ ስለማይችል ነው፡፡

ምርቶች ወይም አገልግሎቶች ከታክሱ "ነጻ" ወይም በዜሮ መጣኔ ሥር ይውላሉ
የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/1994 አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ 2 እና አንቀጽ 8 በዝርዝር ተለይተው የተጠቀሱ ሲሆን እነዚህም አቅርቦቶች (ዕቃዎችና አገልግሎቶች) በዚህ ሠነድ ክፍል ስምንት የተመለከቱትን በመገንዘብ ለይቶ ማወቅ ይቻላል፡፡

ከታክሱ "ነጻ" መሆንና “ በዜሮ ” መጣኔ መካከል ያለው ልዩነት
በዜሮ መጣኔ ታክስ የሚታሰብባቸው አቅርቦቶች (ዕቃዎችና አገልግሎቶች) ለውጭ ገበያ ለሚቀርቡት ሲሆን በታክስ ማዕቀፉ ውስጥ የታቀፉ መሆናቸውን ለመግለጽ በዜሮ ከመቶ የታክስ መጣኔ እንደሚከፈልባቸው ይታሰባሉ፡፡

እነዚህ ምርቶችና አገልግሎቶች በተግባር ምንም ዓይነት ታክስ የማይከፈልባቸው ሲሆኑ ነገር ግን ለምርቶቹ አቅርቦት የተከፈለ የግብዓት የተጨማሪ እሴት ታክስ ለአቅራቢዎቹ ተመላሽ የሚደረግበት ሁኔታ ስላለ ከታክሱ ነጻ ከሆኑት በጣም ይለያል፡፡ ከታክሱ "ነጻ" የሆኑ ምርቶችና አገልግሎቶች ምንም ዓይነት የተጨማሪ እሴት ታክስ አይከፈልባቸውም፣ ለግብዓት የከፈሉት ታክስ ካለም አይታሰብላቸውም /አይቀናነስላቸውም/፡፡ በአጠቃላይ እነዚህ ምርቶችና አገልግሎቶች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ሥርዓት ውጭ ናቸው ማለት ነው፡፡

 
Read More>>
 
Copyright © SNNPRS CBB 2010 All rights reserved
Created by Webmaster
This is the Official SNNPRS Capacity Building Bureau Website